Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አየርላንድ የ446 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት ከአየርላንድ መንግስት ጋር የ446 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሪት ያስሚን ዎሃብረቢ እና በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ኒኮላ በርናን ፈርመዋል።
ስምምነቱ ለኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ ሲባል በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት መካሄዱም ታውቋል።
የድጋፍ ስምምነቱም በአቀጣላይ 10 ሚሊየን ዩሮ (446 ሚሊየን ብር) ሲሆን፥ ለአምስተኛ ምዕራፍ የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር ማስፈፀሚያ የሚውል መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በስምምነቱ በአጠቃላይ ለአምስተኛ ምዕራፍ የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን፥ የምግብ ፍጆታን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ ተገልጿል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.