Fana: At a Speed of Life!

የዳውሮ ዞን ነዋሪዎች የህወሃት ቡድን የፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ ሠልፍ እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ ፣ህዳር 10 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዳውሮ ዞን ነዋሪዎች የሕወሓት ቡድን የፈጸመውን ጥቃትና የሀገር ክህደት በመውገዝ በተርጫ ከተማ ሠላማዊ ሠልፍ እያካሄዱ ነው።

በሰልፉ ከዳውሮ ዞን አስር ወረዳዎችና ከተርጫ ከተማ የተውጣጡ ነዋሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ሰልፈኞቹ መንግስት በጽንፈኛው ሕወሓት ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር ዘመቻ እንደሚደግፉ እየገለጹ ነው፡፡

እንዲሁም “አረመኔው የጥፋት ቡድን ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ ጠላት በመሆኑ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ እንታገላለን” ሲሉ ያረጋገጡት ሰልፈኞቹ፤ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ቡድኑ ያደረሰውን ጥቃት እንደሚያወግዙ የሚገልጹ መፈክሮችን በማሰማት ላይ ናቸው።

በመርሃ ግብሩ ከመከላከያ ሚኒስቴርና ደቡብ ክልል የተውጣጡ አመራሮችም ተገኝተዋል።

ሰልፈኞቹ ለሀገር መከላከያ ያላቸውን አጋርነት ለመግለፅ የእርድ እንስሳት ድጋፍና ደም ልገሳ እንደሚካሄድም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.