Fana: At a Speed of Life!

ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከዳሮር ወረዳ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች በጀረር ዞን ከዳሮር ወረዳ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው።
ውይይቱ በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳይ፣ በሰላም እና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ዙሪያ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
ነዋሪዎቹ በሁለት ዓመት ውስጥ የተገኘውን ሰላም እና የመሰረተ ልማት ጅማሮዎች መልካም እንደሆኑ ገልፀው፤ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ለመበጥበጥ እና ሰላሟን ለማናጋት የሚንቀሳቀሱ የውስጥ እና የውጭ ኃይሎችን እንደሚቃወሙ ገልፀዋል።
እኛ የምንፈልገው ሰላም፣ እድገት፣ ለውጥና እና ብልፅግናን ነው ያሉት የደሮር ነዋሪዎች፥ ይህንን ሊነጥቀን የሚመጣ የትኛውንም አካል ከክልላችን መንግስት፣ ከፌደራል መንግስት እና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆነን እንታገላለን ብለዋል።
በሌላ በኩል የህግ ማስከበር ግዳጅ ላይ ካለው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በማንኛውም መንገድ ከጎኑ ነን ሲሉም አጋርነታቸውን መግለፃቸውን ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.