Fana: At a Speed of Life!

ቀለብ ሰፋሪው ህወሓትና ቀለብተኛው ኦነግ ሸኔ ጀንበር እየጠለቀችባቸው ነው- ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በጁንታው ህወሓት የሚደገፈው ኦነግ ሸኔ ከዚህ በኋላ በኦሮሚያ እድሜ እንደማይኖረው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጀነራል ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ዛሬ እንዳስታወቁት ቀለብተኛው ኦነግ ሸኔ ከዚህ በኋላ የክልሉን ሰላም መንሳት አይችልም፡፡

ሽፍታው በክልሉ የሚያደርሰውን ጥፋት ለመከላከልና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ጠንካራ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

በዚህም 1 መቶ 60 የሚሆኑት ሲደመሰሱ፣ 68 በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተጨማሪም 1 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ለቡድኑ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ እና 1 መቶ 4 የሚሆኑት ከህወሓት የጥፋ ቡድን ጋር በቀጥታ ግንኙነት የነበራቸው መሆኑ ተረጋጦ በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያሉት፡፡

ሽፍታው በሚንቀሳቀስባቸውን ዞኖች የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጠንካራ ስራ እየተሰራ እንዳለም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡

በቦረናና ጉጂ ዞን ቡድኑን ለመያዝ ከአባ ገዳዎችና ነዋሪዎች ጋር እየተሰራ እንዳለም ገልፀዋል፡፡

ቀላቢው ህወሓት ላይ ጀንበር እየጠለቀችበት እንዳለ የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ ቀለብተኛውም ቢሆን መጥፊያው ደርሷል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.