Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ለማክበር ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ተረጋግጧል- ሚኒስትሮቹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ እና ሩሲያን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት በተመለከተ ሚኒስትሮቹ ውይይት አድርገዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን እና የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሀገራቱ በንግድ፣ ኢኮኖሚ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ማስፋት በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል።

እንዲሁም በባህል እና በሰብዓዊ ጉዳዮች ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ምክክር አድርገዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለሰርጌ ላቭሮቭ የፌደራል መንግስት ህገ መንግስትን ለማስከበር በትግራይ ክልል ስለወሰደው እርምጃ ገለፃ አድርገዋል።

ሩሲያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ለማክበር የማይናወጥ አቋም እንዳላት መረጋገጡትን ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው ላይ አንስተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.