Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሀገራት በ2021 መጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንደሚያገኙ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአፍሪካ ሀገራት በፈረንጆቹ 2021 መጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንደሚያገኙ የአፍሪካ ህብረት ልዩ ልዑክ አስታወቀ፡፡

ልዩ ልዑኩ ይህንን ያስታወቀው ከናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂኦፍሪይ ኦኒዬማ ጋር በአቡጃ በዝግ ከመከረ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

በዚሁ ወቅት  “በዓለም ላይ አንድ ሰው እንኳ ኮሮና ቫይረስ ቢገኝበት የትኛውም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም” ያሉት ኦኮንጆ ኢዌላ ለዚህም ታዳጊና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት በተቻለው ፍጥነት ክትባቱን ማግኘት አለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

እንዲሁም ዓለም አቀፉ ጥምረትም ለታዳጊና መካከለኛ ገቢ ላይ ለሚገኙ ሃገራት በፍጥነትና አቅማቸውን ባገናዘበ መልኩ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡

ክትባቱ በሚመጣበት ወቅት በመጀመሪያ ዙር ለወረርሽኑ ተጋላጭ ለሆኑ የለማህበረሰብ ክፍሎች ይሰጣል ተብሏል፡፡

እስካሁን አፍሪካ በወረርሽኙ እንደሌላው አህጉር እንዳልተጠቃች ያነሱት ኦኮንጆ ሀገራት በዚህ ጉዳይ እንዳይዘናጉ ሲሉ መክረዋል፡፡

በአህጉሪቷ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ መድረሱን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል አስታውቋል፡፡

ማዕከሉ በወረርሽኙ ከተያዙት መካከል 1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ማገገማቸውን ገልጾ 54 ሺህ 503 የሚሆኑት ህይወታቸውን እንዳጡ ነው የገለጸው፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.