Fana: At a Speed of Life!

ፌስቡክ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን ኢላማ ያደረጉ ከሩሲያና ከፈረንሳይ የሚነሱ አካውንቶች መዝጋቱ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌስቡክ ኩባንያ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ምርጫ ላይ ያተኮሩ ከሩሲያና ከፈረንሳይ የሚነሱ አካውንቶች መዝጋቱን አስታወቀ፡፡

ፌስቡክ በሦስት ኔትዎርኮች በጥቅሉ 500 የሚደርሱ ከሃገራቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካውንቶችን ነው ያገደው፡፡

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከሁለት ሳምንት በኋላ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደምታደርግ ተገልጿል፡፡

በቅርቡ የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ የታገዱት አካውንቶች የተሳሳቱ መረጃዎችን እያሰራጩ እንደነበር ነው የተጠቀሰው፡፡

ሐሰተኛ አካውንቶችን በመፍጠር እንዲሁም ሐሰተኛ ፎቶግራፎችን በመጠቀም የምርጫ ዘመቻ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ሞክረዋል ተብሏል፡፡

ፌስቡክ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በተጨማሪ 13 የአፍሪካ ሀገራትን ዒላማ ያደረጉ የተሳሳቱ መረጃዎች እንደሚለቀቁ ነው የገለጸው፡፡

ከሃገራቱም መካከል አልጄሪያ፣ ካሜሮን፣ ሊቢያ፣ ሱዳን እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ኩባንያው ጠቅሷል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.