Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በቡኖ በደሌ ዞን ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ ቡኖ በደሌ ዞን እና ከተማ ጉብኝት አደረገ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ትናንት ምሽት በደሌ ከተማ የገቡ ሲሆን ÷ በዛሬው እለት በከተማው እየተገነባ ያለውን አዳሪ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል።
ትምህርት ቤቱ በ167 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ሲሆን÷ ግንባታው 5 ነጥብ 5 በመቶ ላይ ያለ በመሆኑ በቀጣይ በፍጥነት ስራው መከናወን እንዳለበት ወይዘሮ ጫልቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።
እንዲሁም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ በ30 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለውን እና ግንባታው 97 በመቶ የተጠናቀቀውን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንባታም ጎብኝተዋል፡፡
በመቀጠልም ከተለያዩ ቴክኒክ እና ሙያ ተመርቀው የስራ እድል የተፈጠረላቸውን ወጣቶች የጎበኙ ሲሆን ከጥሬ እቃ አቅርቦት ጋር ተያይዞ ያነሱትን ጥያቄ የክልሉ መንግስት ለመፍታት እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል ።
በአፈወርቅ አለሙ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.