Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ግርማ ተመስገን ከቱርክ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ኃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 15 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ተመስገን ከቱርክ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ኃላፊ አኪፍ ካጋታይ ኪሊክ ጋር ተወያዩ።
በውይይቱም አምባሳደር ግርማ በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ እና በቱርክ ምክር ቤቶች አባላት መካከል ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይም ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅት አኪፍ ካጋታይ ኪሊክ ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እና በሃገሪቱ ያሉ ሁኔታዎችን በቅርበት እንደሚከታተሉም ተናግረዋል ፡፡
አያይዘውም በሃገሪቱ የተመለሰውን ሰላም ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል ያላቸውን ተስፋ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.