Fana: At a Speed of Life!

ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ሴቶች በአሰላ ከተማ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ሴቶች በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
በጉብኝቱ የሴቶች አደረጃጀትና ተጠቃሚነት ስራዎች መቃኘታቸው ተገልጿል።

በዚሁ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ ÷የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በአንጻሩ በአፈፃፀም ረገድ ግን ከአካባቢ አካባቢ ልዩነቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

አያይዘውም ሴቶችን በማደራጀት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በመሰራት ላይ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።

አሰላ ከተማ በዘርፉ የተሻሉ ውጤቶችን ማስመዝገቡን የገለጹት ወይዘሮ መሰረት በሌሎች አካባቢዎችም ይህን ለማስፋት ጉብኝቱ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በከተማዋ በተለያዩ መዋቅሮች የተደራጁ ሴቶች በበኩላቸው ÷መደራጀታቸው በህይወታቸውና አኗኗራቸው ለውጥ ማምጣቱን ተናግረዋል።

የአሰላ ከተማ ከንቲባ አቶ ገብሬ ኡርጌሶ ÷የሴቶች ተጠቃሚነት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት መንገድ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አያይዘውም ለከተማዋ ሰላምና እድገት አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።

የልምድ ልውውጥ መድረኩ በኦሮሚያ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮና የኦሮሚያ ብልፅግና ሴቶች ሊግ በጋራ ያዘጋጁት መሆኑም ተመላክቷል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.