Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከመንግስት እና ከግል ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን ማስረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ ነው።

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ይህ አሰራር ተቋማት እና ግለሰቦች ሰራተኞችን ለመቅጠር በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳይታለሉ ይረዳል።

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ሀሰተኛ እና የተሳሳተ የትምህርት ማስረጃን ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ የሚጠይቀው ሂደት ረጅም በመሆኑ አድካሚ ሆኖ ቆይቷል።

አሁን ግን ከተለያዩ ተቋማት ጋር ጥምረት በመፍጠር በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተደራጀ መረጃ ለሚፈልግ አካል ለመሰጠት ስራዎች መጠናቀቃቸውን አሰታውቀዋል።

ስራውንም ለማስጀመር የኤጀንሲው ሰራተኞች በቂ ስልጠና መውሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡

የህግ ተጠያቂነት እንዲኖረውም ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር እንዲሁም ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በጋራ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ስራዎቹ ተጠናቀው በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆኑም ጠቁመዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.