Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መቀመጫቸውን ደቡብ ሱዳን ላደረጉ አለም አቀፍ ሚዲያዎች በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መቀመጫቸውን በደቡብ ሱዳን ላደረጉ አለም አቀፍ ሚዲያዎች በበየነ መረብ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል።
የበየነ መረብ የውይይት መድረኩን ያዘጋጁት በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል አቶ አይሸሽሁም ተካ በደቡብ ሱዳን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በጋራ መሆኑ ተገልጿል።
አምባሳደሩ በደቡብ ሱዳን ለሚገኙ 16 የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ውዝግብን አስመልክተውም አምባሳደር ዲና÷ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ህግና ስርዓትን በማስከበር ተጠምዶ ባለበት ወቅት ሱዳን የኢትጵያ ድንበር ውስጥ ገብታ የኢትዮጵያ ዜጎችን መዝረፍ እና ማፈናቀሏን መጀመሯን ገልጸው ይህንንም እንድታቆም አሳስበዋል።
የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ላይ ያሳየው ወቅታዊ ጠብ የሱዳንን ህዝብ የማይጠቅም ብቻ ሳይሆን በሁለቱ አገራት ህዝቦች መካከል የቆየውን ወዳጅነት እና ግንኙነት አንፀባርቅም ነው ያሉት።
ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ሽምግልና ያቀረቡትን ሁሉ ሀገራቸው አድናቆት እንዳላት የተናገሩት አምባሳደር ዲና ÷ የሱዳን ጦር በኃይል የወሰደውን አካባቢ ለቆ ከወጣ በኋላ ሁለቱ አገራት ነባር አሠራሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይችላል ብለዋል፡፡
የሱዳን መንግስት ዓለም አቀፍ ህጎችን እንዲያከብር እና በሁለቱ አገራት መካከል እርቀ ሰላም መፍትሄ እስከሚገኝ ድረስ ያለውን ሁኔታ ለማስቀጠል በሁለቱ አገራት መካከል በ 1972 የተደረገ ስምምነትንም እንድታከብር አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
የህዳሴ ግድብ ድርድርን አስመልክቶም ሱዳን ከግድቡ ደህንነት ጋር በተያያዘ የምታነሰው ሶስተኛ ወገንን ለመጥቀም በድብቅ የያዘችውን አጀንዳ ለመሸፈን የምታቀርበው ምክንያት ነው ብለዋል።
አምባሳደሩ በትግራይ ክልል የተደረገው የሕግ ማስከበር ሥራ በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸው÷ አሁን የኢትዮጵያ መንግሥትጉዳት የደረሰባቸውን መሠረተ ልማቶችን መልሶ በማቋቋም እና በመገንባት ላይ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ሆኖም በአንዳንድ የዓለም ማህበረሰብ አባላት እና በዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሀሰት መረጃን እያሰራጩ መሆኑን ገልጸዋል ።
በክልሉ ውስጥ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት አምባሳደሩ÷ የፌዴራል መንግስት እንዲሁም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ለማድረስ ከድርጅቶቹ ጋር በቅርበት እየሰሩ ናቸው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.