Fana: At a Speed of Life!

የመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹና ሰላማዊ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል – የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ከወረዳ አመራሮች፤ የፀጥታ አካላትና ከትምህርት ቢሮ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ላይ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማደናቀፍ የጥፋት ሃይሎች ተማሪዎችን ሽፋን በማድረግ ሁከትና ግርግር ለመፍጠር ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል በውይይቱ፡፡

የጥፋት ኃይሎቹ ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳዎችን በማራማድ የመማር ማስተማር ሂደት ለማደናቀፍ የሚያደርጉ አካላትን እንቅስቃሴ ሁሉም ማህበረሰብ ሊከታተለው ይገባል ሲሉም ነው የተናገሩት።

በተለይም የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ አካላት የመማር ማስተማሩ ስራ ሰላማዊ የተረጋጋና ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከናወን በቅንጅት መስራት ይኖርበታል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች በእውቅትና በክህሎት ተማሪዎች ራሳቸውን የሚበቁበት እና ከማንውም ፖለቲካ እንቅስቃሴ ነፃ ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ በዚህ ጉዳይ ላይ የመምህራን ተማሪዎች ወላጆች እና ሌሎች አካላትን ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መሰራት ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ናስር ዩያ የወረዳ አመራሮች የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅና ከማረጋጋት አኳያ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

ወጣቱ በውሸትና በሀሰተኛ ሶሻል ሚዲያ የሚሰራጩ አፍራሽና በሬ ወለድ ሃሳቦች ተጋላጭ እንዳይሆኑ የማስገንዘብ ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥልም ይገባል ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፡ https://www.fanabc.com/

ዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም https://t.me/fanatelevision

ትዊተር https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.