Fana: At a Speed of Life!

125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት በፓናል ውይይት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የኅብረ ብሔራዊ አንድነት አርማ” በሚል መሪ ቃል በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት በዌቢናር ውይይት ተከበረ፡፡
በደቡባዊ አፍሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም የውይይቱ አላማ በደቡባዊ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዓድዋን የድል ስኬት ሚስጥሮች በአግባቡ በመገንዘብ ሕብረታቸውን አጠናክረው ለአገር ልአላዊነት እና ለህዝቦች አንድነት በየተሰማሩበት ድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያግዝ መነሳሳትን መፍጠር እንደሆነ ገልፀዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.