Fana: At a Speed of Life!

በበጀት አመቱ ስድስት ወራት የአቪዬሽን ባለስልጣኑ ለ214 ባለሙያዎች አዲስ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤ.ቢ.ሲ) በበጀት አመቱ ስድስት ወራት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ለ214 ባለሙያዎች አዲስ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ መስጠቱ ተገለፀ፡፡
የባለሰልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አንሙት ለማ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷ በበጀት አመቱ አጋማሽ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሰጠው አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ውስጥ 154 የሚሆነው ለአውሮፕላን አብራሪዎች ሲሆን 60ው ደግሞ ለአውሮፕላን ቴክኒሻኖች ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለ2 ሺህ 857 ባለሙያዎች የፍቃድ እድሳት ማድረጉ ተገልጿል።
ከዚህ ውስጥም 2 ሺህ 156 የሚሆኑት የአውሮፕላን አብራሪዎች ሲሆኑ÷ 701 ለአውሮፕላን ቴክኒሺያኖች መሆኑ ታውቋል።
ከዚህም ባለፈ ባለስልጣኑ ለ4 ሺህ 250 የበረራ ሰራተኞች የአስተናጋጆች የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ዕድሳት መስጠቱን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
በታሪክ አዱኛ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.