Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ያለፉት 6 ወራት የስራ አፈጻጸሙን ገመገመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የ2013 በጀት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል።

የታላቁ የኢትዮጲያ የህዳሴ ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት በጅግጅጋ ከተማ ባካሄደው የግምገማ መድረክ ላይ የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄን፣ የሶማሌ ክልልን ጨምሮ  ከሁሉም ክልሎች፣ ከአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የግምገማ መድረኩ በ2013 የበጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት በዋናው ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱና በየክልሎች የሚገኙ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች የተከናወኑ ስራዎችን ለመገምገምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ተብሏል።

በመድረኩ ላይ የግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎች የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በአፈፃፀሙ ላይ የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻል ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር በቀጣይ ሊሰሩ በሚገቡ ስራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት መካሄዱን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኀን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.