Fana: At a Speed of Life!

ትምህርት ቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የመጠጥ ውሃና የመፀዳጃ ቤት እንዲኖራቸው የሚያስችል መመሪያ ወደ ትግበራ ገባ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትምህርት ቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የመጠጥ ውሃና የመፀዳጃ ቤት እንዲኖራቸው የሚያስችል መመሪያ ወደ ትግበራ ገባ።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ያግዛል የተባለው እና ትምህርት ቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የመጠጥ ውሃና የመፀዳጃ ቤት እንዲኖራቸው የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል።

መመሪያውን የትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒሴፍና ፒ ኤስ አይ በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን ÷ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥም እየተተገበረ መሆኑ ተገልጿል።

ሰነዱን ለማዘጋጀት ዩኒሴፍ በገንዘብና በቴክኒክ ድጋፍ ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን መመሪያው  የጥገና ፣ የዲዛይንና የግንባታን መመሪያንም የያዘ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ÷መመሪያው የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እንደሚያግዝ  ገልፀው መመሪያው እንዲዘጋጅ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር፣ የዩኒሴፍ እና የፒ ኤስ አይ ሃላፊዎች በተገኙበት  የተዘጋጀውን መመሪያ  ርክክብ መደረጉን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.