Fana: At a Speed of Life!

የክልሎች የፍልሰት ትብብር ጥምረት ምስረታ በመከናወን ላይ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የክልል ትብብር ጥምረት በጎንደር፣ አዳማና ይረጋለም ከተሞች መመስረቱን በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጥምረቱ ምስረታ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ተከትሎ ክልሎች የየራሳቸውን የፍልሰት ትብብር ጥምረት እነደሚመሰርቱ በተገለፀው መሰረት የተከናወነ መሆኑ ታውቋል፡፡
በምስረታው በየክልሉ የሚገኙ ቢሮዎች፣ የሀይማኖት ተቋማት ፣መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሲቪል ማህበራት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በመድረኩም የትብብር ጥምረቱ መመስረቻ መመሪያዎችና የ6 ወር እቅድ ታቅዶ የየክልሉ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ምስረታው ተከናውኗል።
የጥምረምስረታ በሰው የመነገድ፣ ሰውን በህገ ወጥ ገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ጠቀሜታቸው የጎላ ከመሆኑ ባሻገር ሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ፍልሰትን ከማስተዳደርና መደበኛ ያልሆነውን ፍልሰት ከመከላከል ከመቆጣጠርና ተጎጂዎችን መልሶ ከማቋቋም አኳያ የየራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ የሚያስችል ነው ተብሏል።
በሌላ በኩል ይህ የምስረታ ሂደት በሌሎች ክልሎችም የሚቀጥል መሆኑን ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.