የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ባለድርሻ አካላት የምክር ቤት ምስረታ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ባለድርሻ አካላት የምክር ቤት ምስረታ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው።
በስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።
ወይዘሮ ዳግማዊት በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ህዝብ እጅ የሚገኘውን አቅም ወደ ስራ ለማዋል በተበተነ መንገድ ሳይሆን በተደራጀ መልኩ መጓዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የሚደራጀው ምክር ቤት በዘርፉ የሚሰጠውን አገልግሎት ነጻ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ ለማድረግ ያስችላል ነው ያሉት ሚኒስትሯ።
ከዚህ ባለፈም የአገልግሎት ሰጪዎችን ተጠያቂነት በማስፈን የህዝቦችን እርካታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።
በመድረኩ ላይ በቀረበው የመነሻ ሰነድ ዙሪያ በተደረገው ውይይት ለሚደራጀው ምክር ቤት ግብዓት የሚሆን ሃሳብ መገኘቱን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በ15 ዓመት ፍኖተ ካርታው ምክር ቤቱን ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ተቋማት ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።