ኢትዮ-ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ይዞታ የማዘዋወር ምዕራፍ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ይዞታ የማዘዋወር አንዱ አካል የሆነው የኢትዮ ቴሌኮም የ40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ በሂደቱ ተሳታፊ የሚፈልጉ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኩባንያዎች የፍላጎት መግለጫ ከነገ ጀምሮ ማስገባት እንደሚችሉ መንግስት አስታውቋል፡፡
የፍላጎት መግለጫው ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን ዝርዝሩም በገንዘብ ሚኒስቴር እና በመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገዕ ላይ እንደሚለቀቅ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ሂደቱ በፋይናንስ፣ በንግድ ሥራ ዕቅድ ፣ በሕግ እና ታክስ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን በሚመለከት ያሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዴሎይት በማማከር እንደ ዋና የግብይት አማካሪ ሆኖ ይሰራልም ነው የተባለው፡፡
የመወዳደሪያ ፍላጎት መግለጫውን ተከትሎ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዕቅድ ጥያቄያቸውን የሚያስገቡ ሲሆን ይህም አጠቃላይ ሂደቱ ወቅቱን የጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና የተስተካከለ አሰራርን በመያዝ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!