1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመላሾች ውስጥ 1 ሺህ 139 ወንዶች፣ 25 ሴቶች፣ 17 ጨቅላ ህጻናት እና 6 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡