Fana: At a Speed of Life!

የ600 ሚሊየን ብር የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 11 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ከ6 የግንባታ ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶች ጋር የ600 ሚሊየን ብር የውል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ÷ የንፁህ ውሃ ፕሮጀክቶች ከዓለም ባንክ በተገኘ 210 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ገልፀዋል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ 55 ወረዳዎችና በ110 የገጠር ቀበሌዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በመገንባት 1 ነጥብ 48 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ በኦሮሚያ  ቦረና ዞን፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ  ወላይታ ዞን፣ በሲዳማ  ዳራ ዞን እና በሶማሌ ክልል በዳሌ ዞን እንደሚገነቡ ተናግረዋል፡፡

ግንባታውን በ1 ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ መደረሱንም ሚኒስትር ዴዔታው  አንስተዋል፡፡

ተቋራጮቹ በገቡት ውል  መሰረት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ሰርተው እንዲያጠናቅቁ ማሳሰባቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.