Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በሚዛን አማን ከተማ ለአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ክልል ደረጃ የ2013 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ለማስጀመር ነው ሚዛን አማን ከተማ የገቡት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዞኑ በሚዛን አማን ከተማ ደቡብ ክልል አቀፍ 3ኛ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን አስጀምረዋል።
በተጨማሪም በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ለአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።
ዞኑ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት የታደለ ሲሆን ÷የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው የአካባቢውን እምቅ አቅም የበለጠ ለማስተዋወቅና ለመጠቀም ትልቅ አቅም ይሆናል ነው የተባለው ።
በተጨማሪም ዞኑ የሸካ፣ የምዕራብ ኦሞ እና ካፋ ዞኖችን እንዲሁም ጋምቤላ ክልልን የሚያዋስን በመሆኑ የአየር ማረፊያ ግንባታው የአካባቢውን የቱሪዝም ተደራሽነት እንደሚያሳድገው ተገልጿል።
ከተማ ባደረጉት ንግግር÷ ሉዓላዊነታችንን ከማስጠበቅ አሁናዊው ድህነታችን አያግደንም ብለዋል።
ነገር ግን ልመናን በማቆም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የምትመች ሀገር እንፈጥራለን ነው ያሉት ።
ልመናን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ አቁመን ራሳችንን ለመቻል በጋራ እንስራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል ።
በተለይም ወጣቶች የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ጸጋ በመጠበቅ ለሀገር ሰላምና አንድነት ዘብ እንዲቆሙ ጠይቀዋል ።
በዓላዛር ታደለ እና ተስፋዬ መሬሳ
ተጨማሪ ምስል ከኦቢኤን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.