Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ዕዝ የ6ኛ ሠርዶ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የአየር መቃወሚያ ሻለቃ በህግ ማስከበሩ ሂደት ስኬታማ ግዳጅ ፈፅሟል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ዕዝ የ6ኛ ሠርዶ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የአየር መቃወሚያ ሻለቃ በህግ ማስከበሩ ግዳጅ ስኬታማ ግዳጅ እንደፈጸመ ዋና አዛዥ ሻለቃ ጋሻው በቀለ ገለፁ።
ሻለቃ ጋሻው ያረምንለት ፣ ያጨድንለት ፣ ትምህርት ቤት የሰራንለት ህዝብ ሲክደን አንድም ቀን ምንም ነገር ያላደረግንለት ህብረተሰብ በየመንገዱ ውሃ እና ምግብ እያበላና እያጠጣ ለሰራዊታችን ያደረገው አቀባበል የተለየ ነበር ብለዋል፡፡
ለቀጣይም ህዝብና መንግስት የሚሰጣቸውን ግዳጅ የበለጠ ለመወጣት ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሆናቸው መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የ2ተኛ ሻምበል አዛዥ ም/መ/አ ፍርዱ ገረመው በበኩላቸው መንግስት እንድንወጣ ካደረገ በሆኋ በምንወጣበት ጊዜ አጥፊው ህዝቡን አስገድዶ እንዲሁም ጦርነቱን መልኩን ቀይሮ ቢመጣም ሰራዊታችን በጥንቃቄ አንድም ህዝብ ሳይመታ በተመረጡ ኢላማዎች ላይ ብቻ በመተኮስ ህዝባዊነቱን ጠብቆ ራሱ ጭምር እየተመታ የነበረውን ደፈጣ በጀግንነት ማስወገድ መቻሉን ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.