Fana: At a Speed of Life!

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠ/ሚ ዐቢይ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ቃል መግባታቸውን አደነቁ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ቃል መግባታቸውን አድንቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በስልክ ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ እንደነበር ነው የዋና ጸኃፊው ቃል አቀባይ ትላንት በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት፡፡
በውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የረድኤት ድርጀቶች በትግራይ ክልል ለሚያደርጉት የሰብዓዊ እርዳታ አስፈለጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል የመገናኛ እና የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትን በአፋጣኝ ለማስጀመርም ቃል ገብተዋል፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ቃል መግባታቸው አድንቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም መንግስት በክልሉ ለሚካሄደው የእርሻ ስራ የተኩስ አቁም መደረጉ እና የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ የበረራ አገልግሎት መፈቀዱ የሚበረታታ መሆኑን ጉቴሬዝ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.