Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ የቀብር ስነ-ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የነበሩት ዘውዴ ተክሉ በተወለዱ በ85 ዓመታቸው በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጿል።

ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ /ማዘጋጃ ቤት/ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ወዳጅ ዘመድ እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተከናውኗል።

ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ በ1973 ዓ.ም በተደረገው 3ኛ ዙር የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ማኅበራት ምርጫ ከንቲባ በመሆን ተመርጠው ከ1973 እስከ 1981 ዓ.ም ድረስ በከንቲባነት አገልግለዋል።

ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ ከአባታቸው ከባሻ ተክሉ አመኑና ከእናታቸው ከወይዘሮ አስካለ ደገፉ በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት በሃረር ዙሪያ አውራጃ በኤጀርሳ ጎሮ ወረዳ ገንደጋራ በሚባል አካባቢ መጋቢት 7 ቀን 1926 ዓ.ም ተወለዱ።

ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ ከወይዘሮ ራሄል ዘውዴ ጋር በመስከረም 1965 ዓ.ም ሕጋዊ ጋብቻን በመመስረት በትዳር በቆዩባቸው 48 ዓመታት ሦስት ሴት ልጆችንና ስድስት የልጅ ልጅ  ለማየት የታደሉ እንደነበሩ ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.