Fana: At a Speed of Life!

ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ይዞ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ይዞ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
 
ተጠርጣሪው የተያዘው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው 22 አንድ ተብሎ በሚጠራው ባቡር ጣቢያ ላይ መሆኑ ነው የተገለጸው።
 
ግለሰቡ በወቅቱ 30 ሺህ 204 የአሜሪካ ዶላር ይዞ ባቡር ሊሳፈር ሲል በባቡር ጣቢያው ላይ ተመድበው ሲሠሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ ከነዶላሩ በቁጥጥር ስር አውለውታል።
 
ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የውጪ ሀገራት ገንዘቦችን በሕገ-ወጥ መንገድ የመመንዘር ወንጀል የኑሮ ውድነት እንዲያሻቅብ ከማድረግ ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።
 
ስለሆነም ህብረተሰቡ ይህንን ሕገ-ወጥ ድርጊት ባለመፈፀም እና የሚፈፅሙ አካላትንም ለሕግ አሳልፎ በመስጠት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.