Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱን በተመለከተ የሚናፈሱ ወሬዎች መሰረተ ቢስ ናቸው-የኢትዮጵያ አየር መንገድ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሳሪያ ወደ ትግራይ ክልል እያጓጓዘ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ሃሰተኛ መሆኑን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ይህን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሳሪያ ወደ ትግራይ ክልል እያጓጓዘ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ በአንዳንድ ግለሰቦች የሚናፈሰውን ወሬ ውድቅ አድርጓል፡፡

በፈረንጆቹ 2020 ህዳር ወር ላይ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎች በሙሉ መቋረጣቸውን ያስታወሰው አየር መንገዱ ከዚያ በኋላ የአየር ክልሉ ለተወሰነ ጊዜ ተከፍቶ ዜጎችን ወደ ክልሉና ወደ አካባቢው በማጓጓዝ አስፈላጊውን አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ገልጿል፡፡

ሆኖም አየር ክልሉ እንደገና ከተዘጋ አንድ ወር እንደሆነው ጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ምንም ዓይነት የጦር መሣሪያም ሆነ ወታደር ወደ ትግራይ እንዳላጓጓዘ አፅንዖት ሰጥጧል፡፡

ለደንበኞቹ፣ ለአጋሮቹ እንዲሁም ለባለድርሻ አካላትም አየር መንገዱ የጦር መሳሪያ ወደ ትግራይ ክልል እያጓጓዘ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ሃሰተኛ ወሬ የስም ማጥፋት ዘመቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱም የአየር ትራንስፖርት ህግጋትን አክብሮ የሚሰራ መሆኑን መግለፁን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.