Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሞትን የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሀገሪቱ የመንግስት ቴሌቪዥን ቀርበው ይፋ አድርገዋል።

ከኬንያ ነጻነት በኋላ ሁለተኛው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን ለ24 ዓመታት በብቸኝነት ሀገሪቱ የመሩት ዳንኤል አራፕ ሞይ በ95 ዓመታችው አርፈዋል።

ፕሬዚዳንት አራፕ ሞይ  ከጆሞ ኬኒያታ ሞት  በኋላ ስልጣን የያዙ ሁለተኛው ፕሬዚዳንት ነበሩ።

ዳንኤል አራፕ ሞይ   ኬንያን ለ24 ዓመታት በአምገነንነት ገዝተዋል ተብለው የሚወቀሱ ሲሆን÷ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይተቻሉ።

የአፍሪካ ትልቁ የፓለቲካ ሰው ማጣት እንዳሳዘናቸው የገለፁት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ÷ዳንኤል አራፕ ሞይ ናይሮቢ ሆስፒታል ውስጥ ህይወታቸው እንዳለፈ ተናግረዋል።

ከፈረንጆቹ 1978 እስከ 2002 ኬንያን ለረጅም ዓመታት በመምራት ቀዳሚ የሆኑት የቀድሞ ፕሬዚዳንት  ከወር በላይ በሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነበር።

ዳንኤል አራፕ ሞይ ምንም እንኳ በአምባገነንነት ቢወቀሱም የሀገር አንድነት ላይ በነበራቸው አቋም በበርካታ ኬንያዊያን ዘንድ ድጋፍ አላቸው።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.