Fana: At a Speed of Life!

የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን መጨረስ የመጀመሪያ ትኩረታችን ሊሆን ይገባል – አቶ ሙስጠፌ ሙህመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን መጨረስ የመጀመሪያ ትኩረታችን ሊሆን ይገባል ሲሉ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙህመድ ገለጹ፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ በክልሉ አስፈፃሚ ቢሮዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ገምግመዋል፡፡
በተያዘው ወር መጨረሻ ላይ በክልሉ የሚካሄደው ምርጫ ከመድረሱ በፊት የልማት ፕሮጀክቶች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ያለመ መድረክ መሆኑን ነው የተገለፀው፡፡
ዛሬ በተደረገው ግምገማ የክልሉ የቢሮ አመራሮች እየተከናወኑ የሚገኙትን ፕሮጀክቶች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙና አፈፃፀማቸውን ያቀረቡ ሲሆን÷ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ በሚያልቁበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሁሉም ቢሮዎች የሚያከናውኑትን ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጨርሱና በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ያላለቁ ፕሮጀክቶች መንስኤና ችግሮች ምን እንደሆኑ መለየት አለባቸው ብለዋል፡፡
አክለውም ባለፈው ዓመት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲሁም አሁን ላይ እየተከናወኑ የሚገኙትን ፕሮጀክቶች ሁኔታና ሂደት ሁሉም ቢሮዎች በአስቸኳይ እንዲያቀርቡ አቅጣጫ መስጠታቸውን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.