የፍቅር ያሸንፋል ማሕበር አባላት የመስቀል አደባባይን አጸዱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የደመራ በዓል ዝግጅት እየተደረገ በሚገኝበት የመስቀል አደባባይ የ“ፍቅር ያሸንፋል ማሕበር” አባላት ተገኝተው ቦታውን በማጽዳት አጋርነታቸውን በሥራ አሳይተዋል።
የማሕበሩ መስራችና ፕሬዚዳንት ሚስባሕ ከድር አባላቱን ይዞ የተገኘው ለረዥም ዓመታት በሀገራችን በዘርና በሃይማኖት ልዩነት እንድንባላ የተሰራብን ተንኮል የማይለያየን ሕዝቦች መሆናችንን ለማሳየት ነው ብሏል።
ከ40 በላይ አባላቱን ይዞ የተገኘው ማሕበሩ ÷ ላለፉት ሦሥት ዓመታት ኢትዮጵያዊያን ያሏቸውን መልካም እሴቶች እንዲያስቀጥሉ እየሰራ ይገኛል።
ማህበሩ የተለያየ እምነት ተከታዮችን በአባልነት ያቀፈ እንደሆነም ሚስባሕ ከድር ተናግሯል፡፡
በሀበነዮም ሲሳይ