ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳ በመካከላቸው የነበረውን የዜጎች የጉዞ ቪዛ አስቀሩ
አዲሰ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡጋንዳውያንና ደቡብ ሱዳናውያን ወደየአገሮቹ ጉዞ ሲያደርጉ ይጠየቅ የነበረውን ቪዛ ማስቀረታቸው ተገለጸ።
ኡጋንዳ ቀደም ሲል በመስከረም ወር የቪዛ ጥያቄን ያስቀረች ሲሆን÷ ደቡብ ሱዳንም በተመሳሳይ ኡጋንዳውያን ያለቪዛ እንዲገቡ ፈቅዳለች፡፡
የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደንግ ዳው ደንግ እንዳረጋገጡት÷ ሀገራቸው ውሳኔውን ያሳለፈችው የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጥያቄን ተከትሎ ነው፡፡
ደቡብ ሱዳን በቅርቡ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ሃገራትን የተቀላቀለች ሲሆን÷ በሃገራቱ መካከል ባለው ስምምነት የሰዎች እና የሰራተኛ ነፃ ዝውውርን ያበረታታል፡፡
ኡጋንዳ፣ ኬኒያ፣ ታንዛኒያ፣ ርዋንዳ እና ብሩንዲ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ሀገራት ናቸው፡፡
ደቡብ ሱዳን የአፍሪካ ማህበረሰብን የተቀላቀለችው እ.አ.አ በ2016 ሲሆን÷ የጋራ ገበያ የመሳሰሉ የማህበረሰብ ተግባራትን ለመቀላቀል ዘግይታለች፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!