Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሕዝብና የጸጥታ መዋቅሩ ቅንጅታዊ ስራ በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ለውጥ አምጥቷል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ መንግስት፣ ሕዝብና የጸጥታ መዋቅሩ ተቀናጅተው በመስራታቸው በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ለውጥ መምጣቱን የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።
 
የመዲናዋ የተለያዩ ሕዝባዊ አደረጃጀቶች የተሳተፉበት በሠላም ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
 
የከተማዋ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ተፈራ፥ ሰላም ለማረጋገጥ የመንግስት፣ የሕዝቡና የጸጥታ አካላት ትብብር በተሻለ ደረጃ እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል።
 
አስተዳደሩ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ የሚችለው በሕዝብ ተሳትፎ መሆኑን በማመኑ ነዋሪውን እያሳተፈ ነው ብለዋል።
 
ሽብርተኞቹ ህወሓትና ሸኔ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት እንዳያውኩ ለማድረግ ነዋሪው አጠራጣሪ ነገሮችን በንቃት እንደሚከታተልም ገልጸዋል።
 
በዚህ ሂደት በቡድኖቹ ለመፈፀም የታሰቡ እኩይ ሴራዎች መክሸፋቸውንም ነው የገለጹት።
 
ከሽብርተኞቹ ተለዋዋጭ እንቅስቃሴ አንጻር የከተማዋ ነዋሪ ከሌላው ጊዜ በተሻለ ደረጃ የፀጥታውን ሁኔታ መከታተል እንዳለበትም አሳስበዋል።
 
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሸነር ጌቱ አራጋው በበኩላቸው፥ ኅብረተሰቡ በየአካባቢው ለጸጥታ ስጋት የሚሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት ፈጥኖ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል።
 
በልደታ ክፍለ ከተማ በሶስቱ አካላት የተሳካ ጥምረት ለውጥ መምጣቱም ያረጋገጡት ደግሞ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰግደው ሃይለጊዮርጊስ ናቸው።
 
በቀጣይም ይህ ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.