Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በውጭ ሃገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአሜሪካ እና ካናዳ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በዋናነት ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ እና በዚህ ፈታኝ ወቅት መንግሥትና ቤተ ክርስቲያኒቱ በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሉ መስኮች ላይ ለመምከር ያለመ ነው።

አቶ ደመቀ በዚህ ወቅት በአሸባሪው ህወሃት በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የተጋረጡ ችግሮችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

አያይዘውም መላው ኢትዮጵያውያን አሸባሪውን ቡድን ለመዋጋት አንድ መሆን እና መተባበር እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የኢትዮጵያን ሁኔታ አስመልክቶ ከውጪ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊዎች፣ ከአሜሪካ ሴኔት አባላት እና ከአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ጋር ተደጋጋሚ እና የተለያዩ ውይይቶችን ማድረጋቸዉን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.