Fana: At a Speed of Life!

ለመስኖ ልማት ስራዎች ውጤታማነት ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በርካታ ቢሊየን ብር እያወጣች የምትገነባቸው የመስኖ ልማት ስራዎች የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ መንግስት ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ የግብርና ምሁራን ገለጹ።
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ተመራማሪ ዶክተር ተስፋዬ መላክ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ጥናትና የግብርና ምሁር ፕሮፌሰር በላይ ስማኔ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ የመስኖ ልማት ስራ በምግብ እራስን ለመቻልና ከጥገኝነት ለመላቀቅ ትልቁን ድርሻ የሚወስድ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
በመሆኑም በመስኖ ግንባታ ዘርፎች ላይ የሚስተዋሉ የግንባታ ክፍተቶችንና ከአፈር አይነቶች ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ መሥራት እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት ምሁራኑ።
የግብርና ምርምር ባለሙያው ዶክተር ኤርሚያስ አባተም÷ ግብርናውን ማዘመን ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት ማሳደግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሀገሪቱን ከጫና ለመታደግና የተትረፈረፈ ምርት ለማግኘት የመስኖ ሥራዎች ልዩ ትኩረት ይሻሉም ነው ያሉት ምሁራኑ።
ለዚህም ዘርፉ በሙያው ባለቤቶች በቅንጅት ቢመራ እና ተጠያቂነት ቢረጋገጥ በግንባታውም ይሁን በማልማቱ ረገድ የተሻለ ስኬት እንደሚመጣም ነው ምሁራኑ ያብራሩት።
ምሁራኑ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑ ተግባራት መከወንና በጊዜ መጠናቀቅ ያለባቸው በእቅድ ወቅት ሊሆን እንደሚገባም የሀገራትን ተሞክሮ በማንሳት አስረድተዋል።
በአጠቃላይ የመስኖ አውታሮች ውጤታማ እንዲሆኑ የተፈጥሮ ሀብት ስራ ላይ ማህበረሰቡ ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል ሲሉ ምሁራኑ አሳስበዋል።
በሙሀመድ አሊ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
No photo description available.
0
People reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.