Fana: At a Speed of Life!

ሀገርን ከእነ ሙሉ ክብሯ ለማቆየት ያለንን አማራጭ ሁሉ እንጠቀማለን – የደቡብ ክልል መስተዳድር

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መላው የደቡብ ክልል ህዝቦች እና አመራሮች ሀገርን ለማዳን ለሚደረገው ፍልሚያ ከሁሉ ተግባር ቅድሚያ ሰጥተው እንዲረባረቡ፣ ወጣቶች ጀግናው የመከላከያ ሃይላችንን እንዲቀላቀሉና ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ፀጥታ እንዲጠብቁ፣ መላው ህዝባችን ጠላትን ለመመከት ሁሉን አቀፍ ድጋፋቸው እንዲያጠናክሩና አካባቢያቸውን ከሰርጎ ገቦች እንዲጠብቁ ውሳኔ አስተላልፏል።
የደቡብ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፡
የክልላችን ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን አሸባሪው የትህነግ ሴራ በማክሸፍ የሀገራችንን ህልውና በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ይሆናሉ።
በተንኮል ተውልዶ በሴራ ፖለቲካ ጥርሱን የነቀለው ራሱን የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሰየመው ዘራፊና አጥፊ ቡድን ለ27 አመታት ሙሉ በክልሉ ህዝቦች ብሎም በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመው በደልና ክህደት ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።
ይህ መርዛማና እኩይ ተግባሩ ባንገፈገፋቸው መላው ኢትዮጵያውያን መራር ትግል ከህዝቦች ጫንቃ ላይ እንዲወርድ የተደረገው አሸባሪው ቡድን ያለፉት ሶስት አመታት የለውጥ ሂደታችንን ለመቀልበስ ያልሸረበው ሴራ አልነበረም።
በክልላችን በዚህ የሽብር ቡድን አቀናባሪነት በተከሰቱ ግጭቶች የበርካታ ዜጎቻችን ህይወት ተቀጥፏል፣ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል፣ ዜጎች ተፈናቅለዋል፣ ዘርፈ ብዙ ጉዳት አድርሷል።
በመላ ሀገሪቱ ሰላማዊ ዜጎችን በመጨፍጨፍ፣ የእርስ በርስ ፍጅቶችን በመጠንሰስ፣ ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር የሀገራችንን ቀንደኛ ጠላትና ባንዳ መሆኑን በተግባር አሳይቷል።
ይህ በቀቢጸ ተስፋ የተሞላ ቡድን አሁንም ይህን እኩይ ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል በአማራና አፋር ክልል ህዝቦች የማያቋርጥ የህልውና ስጋት ደቅኖ ይገኛል። ይህ ህገወጥ ቡድን ጠቤ ከተወሰኑ ክፍሎች ጋር ነው ቢልም ዋነኛ ግቡ ሀገራችንን ማፍረስ እንደሆነ እሙን ነው።
ይህም ብቻ ሳይሆን ዛሬ በአማራና አፋር ክልሎች የጀመረውን የሽብር፣ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ መድፈር፣ ዘረፋና የሌብነት ተግባር በእነዚህ አካባቢዎች ተገድቦ የሚቀር እንዳልሆነ መታወቅ አለበት።
ይህ ሰውበላና ዘራፊ ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ እድሜ ልክ ለመበደል እና የራሱን ጀሌዎች ብቻ በሀብት ማማ ላይ ከፍ ለማድረግ ሩቅ አልሞ ቢጓዝም ለውጥ ናፋቂው እና በቡድኑ የደረሰበት በደል ያንገሸገሸው የሀገራችን ህዝብ ባሳየው ታላቅ ትግል አሸባሪው ቡድን ከማዕከላዊ መንግስት በስልጣን እንዲገለል ተደርጓል።
ላለፉት 27 ዓመታት የህዝባችንን ደም እንደ መዥገር ተጣብቆ ሲመጥ የነበረው ይህ ጁንታ ቡድን ዛሬም እኔ ያልነገስኩባት ሃገር ትፍረስ፣ ለእኔ ያልተገዛ ህዝብ ይጥፋ በሚል ማንነቱን ያሳየ እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋና ውድመት እያደረስ ይገኛል።
ይህ የጥፋት ቡድን ትውልድን ሲያመክን የኖረ፣ ከውጭ ጠላት በላይ የኢትዮጵያን ክብር ያዋረደ ሰው በላ ስርአት እስከወዲያኛው ታሪክ ሆኖ እንዲቀር የጠነከረ አንድነት ያስፈልጋል።
ይህንን የሽብር ቡድን አምርሮ መዋጋት ደግሞ አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ መላው የክልላችን ህዝቦች ቡድኑን በመገርሰስ ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ የክልሉ መንግስት ጥሪውን ማስተላለፍ ይወዳል።
ጀግኖች አባቶቻችን በደም እና በአጥንት ያቆዩልንን ገናና ሀገር ማንም ከምድር ተነስቶ በመሰረተው ተራ የሽብር ቡድን ሊያፈርስ አይችልም።
ሀገርን ከብተና ዜጎቻችንን ደግሞ ከእልቂት መታደግ የምንችለው በጀግኖች ወጣቶቻችን እና በመላው ህዝባችን መራራ ትግል ብቻ ነው።
መታሰር፣ መሰደድ፣ መሞት፣ ተገዶ መደፈር፣ በአንጡራ ላብ ያፈራነው ሀብት በወሮ በላው ቡድን መዘረፍ እና መሰል የሰቆቃ ጊዜያት እንዲያበቃ ለሀገራችን ህልውና በቁጭት እና በአትንኩኝ ባይነት ስሜት መታገል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።
ዛሬ እንዳሻን የምንኖርባትን ሀገር እንደው በዋዛ አልተረከብንም ጀግኖች አባቶቻችን በዱር በገደሉ እየተዋደቁ የአሁኑን ማንነታችንን አስረክበውናል።
ይህችን ገናና ሀገር ከእነ ሙሉ ክብሯ ለማቆየት ያለንን አማራጭ ሁሉ በመጠቀም ይህንን ሰው በላ ቡድን ለአንድና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰስ ይጠበቅብናል።
ውጊያችን ከጁንታው ጋር ብቻ ሳይሆን ከዚህ አጥፊ ቡድን ኢትዮጵያን የመበተን እኩይ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከተጋቡ የውጭ እና የውስጥ የጥፋት ተባባሪዎች ጋር ጭምር እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን።
ስለሆነም መላው የክልላችን ህዝቦች የሽብር ቡድኑን ተላላኪዎችና ሰርጎ ገቦችን መከታተልና የአካባቢያችሁን ከምንም ጊዜ በላይ ነቅታችሁ እንድትጠብቁ፣ በግንባር እየተዋደቀ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለክልል ልዩ ሃይሎች፣ ለሚሊሻዎችና ለተፈናቀሉ ወገኖች ስታደርጉ የቆያችሁትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እንጠይቃለን።
በመጨረሻም በክልላችን ያለንን ብዝሀነት በመጠቀም ሊያባላን ያሰፈሰፈውን የጠላት ሃይል ግብአተ መሬት ለመፈጸም መላው ህዝባችን በአንድነት እንዲንቀሳቀስ፣ የክልላችን ወጣቶችም ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት እንዲቀላቀሉ፣ አካባቢያቸውን ተደራጅተው በንቃት እንዲጠብቁ፣ በየደረጃው ያለው አመራርም የክልሉን ጸጥታ አካላት፣ ወጣቶች እና ምልዓተ ህዝቡን በማስተባበር በግንባር ቀደምትነት እንዲረባረብና ለማይቀረው ድል ያለንን ሁሉ ምንም ሳናስቀር ጠላትን ለመመከትና ሀገርን ለማዳን በማዋል ለሚደረገው ፍልሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ወስኗል፡፡
ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትቀጥላለች!
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of outdoors
0
People reached
589
Engagements
Distribution Score
Boost Post
521
27 Comments
40 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.