Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራ፣ ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ዶክተር ኦስማን ዲዮን እና ባልደረቦቻቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም ወይዘሮ ጫልቱ በኢትዮጵያ የከተሞችን መሰረተ ልማት ለማሻሻልና የከተማን ነዋሪዎች ሕይወት ለመለወጥ በመካሄድ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በመደገፍ የዓለም ባንክ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

መንግስት በባንኩ ድጋፍ የሚከናወኑ የከተሞች የምግብ ዋስትና እንዲሁም ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እያከናወነ መሆኑንም ገልጸውላቸዋል፡፡

ሚኒስትሯ አያይዘውም ሚኒስቴሩ በአሁኑ ወቅት የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደተግባር መግባቱን ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እያከናወናቸው ያሉ ፕሮጀክቶችን አድንቀው በቀጣይም ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.