Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በጦር ወንጀል የሚጠረጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳልፋ ለመስጠት ቃል ገባች

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2014 (ኤፍቢ ሲ) እስራኤል የጦር ወንጀል ፈጽመው ወደ አገሯ የገቡ ተጠርጣሪ ግለሰቦችን አሳልፋ ለመስጠት ቃል መግባቷ ተዘገበ፡፡

በቅርቡ በአውሮፕላን ወደ እስራኤል ከገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል የጦር ወንጀል ፈጽመው መገኘታቸው ከታወቀ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ እስራኤል መግለጿን ቻናል 13 የተሰኘው የአገሪቱ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

እስራኤል ይህን አቋም የያዘችውም ጠቅላይ ሚኒስትርዐቢይ አህመድ ከእስራኤሉ አቻቸው በጉዳዩ ላይ በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ እንደሆነም በዘገባው ተመልክቷል።

ቻናል 13 በጉዳዩ ላይ የተሳተፈውን የደህንነት ምንጭ ጠቅሶ እንደዘገበው ÷ ባለፈው ዓመት ወደ እስራኤል ከገቡት ከ2ሺህ በላይ ሰዎች መካከል ቢያንስ አራት መኮንኖች በንፁሃን ዜጎች ጭፍጨፋ ተሳትፈዋል ተብለው ተጠርጥረዋል።

እስራኤል ባለፈው ዓመት ወደ ሀገሯ ከገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል አብዛኞቹን እውነተኛ ማንነት ለማወቅ ችግር ሊገጥማት እንደሚችልም ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ ፡- ዘ ታይምስ ኦፍ እስራዔል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.