በድሬዳዋ ማንኛውም አካል የጦር መሳሪያውን እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ፖሊስ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልከቶ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
ማንኛውም በድሬዳዋ ከተማ እና ገጠር ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ ፣ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትና መስሪያ ቤት በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ፍቃድ ቢኖረውም ባይኖረውም በአቅራቢያው በሚገኝ የቀጠናው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በግንባር በመሄድ ማስመዝገብ እንዳለበት አሳስቧል፡፡
ፖሊስ እንዳስታወቀው ከህዳር 2 እስከ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ፣ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትና መስሪያ ቤት በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ሳያስመዘግብ ቢቀር ተገቢውን እርምጃ ይወሰድበታል ማለቱን የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል::
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!