Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በኬንያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት የቀብር ስነ ስርዓት እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመራ ልዑካን በኬንያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ብሔራዊ የቀብር ስነ-ስርዓት እየተሳተፈ ነው።
 
በንያዮ ስታድየም እየተካሄደ በሚገኘው ስነ ስርዓት የሀገሪቱ ፕሬዚዳን አሁሩ ኬንያት ፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌ ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ተገኝተዋል።
 
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዛሬ ጠዋት ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኬንያ ቱሪዝምና ዱር ሃብት ሚኒስትር ነጂብ ባላላ ፣ በኬንያ የኢፌዴሪ አምባሳደር መለስ ዓለም፣ የኤምባሲው ዲፕሎማቶች እና ሌሎች የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
 
ከኬንያ ነጻነት በኋላ ሁለተኛው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን ለ24 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት ዳንኤል አራፕ ሞይ ባሳለፍነው ሳምንት በ95 ዓመታችው ከዚህ ዓለም በሞት መለታቸው ይታወሳል።
 
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም ለኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በላኩት የሀዘን መግለጫ በቀድሞው ፕሬዚደንት ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በኢትዮጵያ ሕዝብና በራሳቸው ስም መግለፃቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.