Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ወደየግንባሩ ተንቀሳቀሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን 12 አባላት ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በ8 ግንባሮች ድጋፍና ቅስቀሳ ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል።
 
የሞረትና ጅሩ ወረዳ ሕዝብ የምክር ቤት አባል ወይዘሮ ታለፍ ፍታወቅ÷ የዘመቻው አካል በመሆን ሕዝቡን በማስተባበር ጠላትን በጋራ በመመከት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት አለብን ብለዋል፡፡
 
ጠላት በሚነዛው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡ ሳይደናገር ከመንግሥትና ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን ለሠራዊቱ የቁሳቁስ፣ የስንቅና ትጥቅ በማቅርብ ደጀን እንዲሆንና አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ የግንዛቤ መፍጠር ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
 
የመንዝ ቀያ ፣ ጌራና የመሐል ሜዳ ከተማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ አቶ ወንድወሰን አድማሴ በበኩላቸው÷ጦርነቱ እንደ ሕዝብ ነው የተከፈተብን፤ ይህንን ጦርነት እንደ ሕዝብ መመከት ይጠብቅብናል ብለዋል፡፡
 
የህልውና ዘመቻው በስኬት እንዲጠናቀቅም ከሕዝባችን ጎን ቆመናል ያሉት አቶ ወንድወሰን ÷ከዘመቻው ባልተናነሰም በወቅቱ የዘማች ሚሊሻ አባላትንና አጠቃላይ ሰብል መሰብሰብ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
 
የመንግሥት ሠራተኛው ፣ ነጋዴው ፣ አርሶ አደሩና መላው ሕዝብ በተባበረ ክንድ ጠላት በገባበት ተቀብሮ እዲቀር እና ታሪካዊ ድል ለመሥራት በቅንጅት መስራት ይጠበቅታል ማለታቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.