Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ ለተፈናቃዮች 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሚድዋይቭስ ማህበር ለተፈናቀሉ ወገኖች አገልግሎት የሚውል 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ማኅበሩ በአማራ ክልል በሽብር ቡድኑ ህወሓት ወረራ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ እናቶችና ህጻናት ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡
 
የማህበሩፕሬዚዳንት አቶ ዘነበ አካሉ÷በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ እናቶችና ህጻናት እንዲሁም ለጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውል ወተት፣ የህክምና ቁሳቁስ እና መድሃኒት ድጋፍ ማድረጋቸውንገልጸዋል፡፡
 
ድጋፉም የተለያዩ አጋር ድርጅቶች በማስተባበር የተገኘ እንደሆነ መግለጻቸውን ከጎንደር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.