Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግስት 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ወጪ በማድረግ ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቧል- የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግስት ከሌሎች ጉዳዮች በማስቀደም በትግራይ ክልል 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ወጪ በማድረግ ሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረቡን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ፅህፈት ቤቱ በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር እርምጃውን ተከትሎ እየቀረቡ ስላሉ የሰብዓዊ ድጋፎች እና ሌሎች ስራዎችን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው የፌዴራል መንግስት በክልሉ ለ3 ነጥብ 8 ሚሊየን ተጠቃሚዎች የሚያቀርበውን የምግብ ድጋፍ ወደ 780 ሺህ 534 ኩንታል አሳድጓል ብሏል።

በክልሉ ምግብ ነክ ላልሆኑ ጉዳዮች የፌዴራል መንግስት 80 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዳደረገም መግለጫው አመልክቷል።

በተመሳሳይ 31 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸው የመጠጥ ውሃ መስመሮችን ለማስተካከል የተለያዩ ስራዎች ተከናውነዋል ተብሏል።

በጤናው ዘርፍም 20 ሆስፒታሎች እና 71 ጤና ተቋማትን ወደ ስራ በማስገባት ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በዚህም ለድንገተኛ ህክምና ከቀረቡት ተሽከርካሪዎች እና ኮሙዪፒውተሮች ባሻገር በ199 ሚሊየን ብር የህክምና ቁሳቀሶች አቅርቦት መከናወኑን ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል።

በክልሉ 96 ሚሊየን ብር በጀት በመያዝ ጥገናዎችን በማድረግ እና አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶችን በማድረግ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.