Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
የአውሮፓ ህብረት ትብብር የኢትዮጵያ ኃላፊ ስቴፋን ሎክ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ጉዞ እንዲሳካ ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ስቴፋን ሎክ አረጋግጠዋል።
ዶክተር በለጠ ሞላ በበኩላቸው÷የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬት እያደረገ ስላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የአውሮፓ ህብረት በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በቴክኒክና በገንዘብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.