Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራዎች የተሳተፉበት የጎዳና ላይ የእግር ጉዞ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተደረገላቸውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የመጡ የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች የተሳተፉበት የእግር ጉዞ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጰያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ያደረጉትን ጥሪ ተቀብለው በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚኖሩ በርካታ የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች ወደ ሀገራቸው መምጣታቸው ተጠቅሷል።

በክልሉ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች የሚሳተፉበት የተለያዩ መርሀ ግብሮች እየተዘጋጁ ሲሆን ፥ በዛሬው እለትም የጎዳና ላይ የእግር ጉዞ ተካሂዷል።

በክልሉ የማርሽ ባንድ በመታገዝ በከተማው ዋና መንገዶች ላይ በተካሄደው የእግር ጉዞ የሶማሌ ክልል የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ ጠይብ አህመድን ጨምሮ የቢሮ ምክትል ሀላፊዎች እና የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች መሳተፋቸውን ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.