Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፈረንስ እና አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፈረንስ እና አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።

አውደ ርዕዩ “ቡናን ከምድረ ቀደምት ሀገር” በሚል መሪ ቃል ነው ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚከበረው።

በአውደ ርዕዩ ላይ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን እና የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የቡና አምራቾችን እና ገዥዎችን በቀጥታ በማገናኘት የሚኖራቸውን ትስስር ይበልጥ ማጠናከር ያስችላል በተባለው አውደ ርዕይ ላይ፥ ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ የቡና ገዥዎች እና የቡና ዘርፍ ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛል።

በመድረኩ የኢትዮጵያን ቡና በዓለም አቀፍ መድረኮች ለማስተዋወቅ የሚያገለግለው አቃፊ ምልክት (ብራንድ ሎጎ) ይፋ ተደርጓል።

በአውደ ርዕዩ ላይ ከ400 በላይ የሀገር ውስጥ ተሳታፊዎች 56 የሚሆኑ ምርቶቻቸውን ለዕይታ የሚያቀርቡ ይሆናል።

በትግስት አብርሃም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.