Fana: At a Speed of Life!

ሁዋዌ ኢትዮጵያ የምታዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ እንደሚደግፍ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁዋዌ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የምታዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ እንደሚደግፍ ገልጿል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ከሁዋዌ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ቻርለስ ዲንግ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በውይይታቸውም ሁዋዌ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የምታዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በገንዘብና በቴክኒክ ጉዳዮች እንደሚደገፍ ምክትል ስራ አስጻሚው ቻርለስ ዲንግ ተናግረዋል።
ተቋማቸው በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከመንግስትእና ከግሉን ዘርፍ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚፈልግም ነው የገለጹት፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በበኩላቸው÷ ሁዋዌ ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ዝግጅትን ለመደገፍ ቃል በመግባቱ ምስጋና አቅርበዋል።
ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ግሩፕ በዓለም ላይ ካሉት ሰራተኞቹ ውስጥ ኢትዮጵያውያን በጣም ጥቂት ናቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷ተቋሙ ኢትዮጵያውያንን ማሳተፍ ላይ በትኩረት እንዲሰራም ጠይቀዋል።
ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ግሩፖ በዓለም ላይ ከ197 ሺህ በላይ ሰራተኞች እንዳሉት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.