Fana: At a Speed of Life!

ለኮቪድ 19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኮቪድ 19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አቋቁመዋል።

መንግሥት ከፍ ያለ በጀት መድቦ አስቸጋሪ ነገሮች ሲከሰቱ ለመቋቋም የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል ተብሏል።

ሆኖም እንደዚህ አይነት ተግባራት የእያንዳንዱን ግለሰብ አስተዋጽኦ የሚፈልጉ መሆናቸው ነው የተጠቆመው።

እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ ስናልፍ፣ በድል አድራጊነት ለመወጣት የሚያስችሉን በኅብረት እና በሚገባ በመቀናጀት የምናደርጋቸው ጥረቶች ብቻ ናቸው ተብሏል።

ተረጋግቶ አስተዋጽኦ ማድረግን በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደመዛቸውን ለብሔራዊ የኮቪድ 19 የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ መለገሳቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.