Fana: At a Speed of Life!

የኤረር መጠጥ ውኃ ፕሮጀክትን በግንቦት ወር መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ224 ሚሊየን ብር የማስፋፊያ ግንባታ እየተከናወነለት የሚገኘው የኤረር መጠጥ ውኃ ፕሮጀክትን በግንቦት ወር መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የኤረር መጠጥ ውኃ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል፡፡

የውኃ ፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ በከተማዋ የመጠጥ ውኃ ችግርን እንደሚቅፍ አቶ ኦርዲን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃም ክትትልና ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የክልሉ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ሥራ አስኪያጅ ዲኔ ረመዳን ፕሮጀክቱ በ224 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ መሆኑን ጠቅሰው÷ ቀደም ሲል ከነበሩት ሰባት ጉድጓዶች ተጨማሪ ሶስት አዳዲስ የውኃ ጉድጓዶች ቁፋሮና የኤልክትሮ መካኒካል ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሁለት የውሃ ማጣሪያ ሲስተም እንደተገነባለት አመልክተው፤ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በቀን 3 ሺህ ሜትር ኪዩቢክ ውኃ ይሰጥ የነበረውን ወደ 7 ሺህ 500 ሜትር ኪዩቢክ ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

የውኃ ፕሮጀክቱ ግንባታ በግንቦት ወር መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቀቅም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.