Fana: At a Speed of Life!

ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የችግኝና የመትከያ ቦታ ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የችግኝና የመትከያ ቦታ ዝግጅት መጠናቀቁን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በነገው ዕለት እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ይፋ ማድጋቸው ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤልያስ እንደገለጹት÷ ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ 6 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል የችግኝና የመትከያ ቦታ ዝግጅት ተጠናቋል።

በመንግሥት ችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች፣ በማህበር በተደራጁ ወጣቶች እና በግለሰቦች የተዘጋጁ በቂ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መሆናቸውንንም አረጋግጠዋል፡፡

ለችግኝ መትከልና ለመጽደቅ አመቺ በሆነ መሬት ላይ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች መዘጋጀታቸውን ጠቁመው÷ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት እንደሚያስጀምሩት ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.